Skip to main content
02

ባለፉት አመታት እንደ ሀገር የተተከሉት 48 ቢሊዮን ችግኞች ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው፦ አባስ መሀመድ (ዶ/ር) 

ሐምሌ 27፣ 2018 ዓ/ም ቡታጅራ ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ መልዕክት በምስራቅ ጉራጌ ዞን ደቡብ ሶዶ ወረዳ ዳሙ ሁለት ቀበሌ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል።

 የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አባስ መሀመድ (ዶ/ር) በመርኃ ግብሩ እንደገለጽት ባለፉት አመታት እንደ ሀገር የተከልናቸው 48 ቢሊዮን ችግኞች በየአከባቢዉ ስነ-ምህዳርን በማሻሻል ምድርን አረንጓዴ በማልበስ በተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ተችሏል ብለዋል። ችግኞችን መተከል ብቻ ሳይሆን የተተከሉትን በመንከባከብ የሚፈለገዉን ጥቅም እንዲሰጡ ተንከባክቦ የማቆየት ከሁሉም አካል እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል። 

የምስራቅ ጉራጌ ዞን ም/አስተዳዳሪና ግብር መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሱ አበጋዝ በ2018 በጀት ዓመት የአረንጓዴ አሸራ መርሃ ግብር ከ33.5 ሚሊዮን በላይ ችግኝኞች እንደ ምስራቅ ጉራጌ ዞን ለመተትከል የተጀመረው የችግኝ ተከላ እስከ አሁን ድረስ ከ14 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸው ገልፀዋል። በዛሬው እለትም እንደ ሀገር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል ከ800 ሚላዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል በታወጀው የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ እንደ ምስራቅ ጉራጌ ዞን በ15 የተከላ ስፍራዎች ከ876 ሺ በላይ የተለያዩ ጠቀሜታ ያለቸው የደንና የፍራፍሬ ችግኞች በአንድ ጀንበር ይተከላሉ ብለዋል። በመትከል በጋራ እንደተረባረብን የተተከሉትም ተንከባኮቦ ለፍሬ ማብቃት እንደሚጠበቅ አሳውቀዋል። 

በመርኃ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ባዩሽ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መላኩ ብርሀኔ ሌሎች የዞን እና የወረዳ አመራሮችና የቀሌዉ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።