Skip to main content
01

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 14 ነጥብ 86 ቢሊየን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ ፕሮጀክቶች ፈቃድ ወስደዋል::

 በበጀት ዓመቱ ያለፉት ወራት14 ነጥብ 86 ቢሊየን ብር ካፒታል ላስመዘገቡ 221 ፕሮጀክቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ። 

ፈቃድ የተሰጠባቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎችም 90 በግብርና፣ 72 በአገልግሎት እንዲሁም 59 በኢንዱስትሪ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ አባስ መሐመድ (ዶ/ር) ። 

የኢንቨስትመንት ፈቃድ ካወጡት ፕሮጀክቶች መካከል 2 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ያስመዘገቡት 34 ዳያስፖራ ባለሃብቶች መሆናቸውንም አመላክተዋል። በአጠቃላይ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ያወጡት ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ ሲገቡ ለ33 ሺህ 885 ዜጎች ቋሚና ጊዚያዊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጠሩም ጠቁመዋል። 

በሌላ በኩል በዘጠኝ ወራት ወደ 9 ቢሊየን 445 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ካፒታል ያስመዘገቡ 106 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች መስፈርቱን አሟልተው የጠየቁት መሬት ተላልፎላቸው ወደ ተግባር እንዲገቡ በክልሉ መንግሥት ውሳኔ መሰጠቱንም አንስተዋል።